Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በድሬ ዳዋ የምትመሰርተው ነፃ የንግድ ቀጠና የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ በጥሩ ደረጃ ላይ ነው- ወ/ሮ ዳግማዊ ሞገስ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የምትመሰርተው ነፃ የንግድ ቀጠና የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊ ሞገስ ገለፁ፡፡
ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ነፃ የንግድ ቀጠናውን እውን ለማድረግ እየሰራ ከሚገኘው የጥናት ቡድን እና ከፌዴራል የሥራ ኃላፊዎች ጋር በነፃ የንግድ ቀጠናው ምስረታ ላይ እየተከናወኑ ባሉ ሥራዎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
የሎጂስቲክስ ትራንስፎርሜሽን ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ እና የጥናት ቡድኑ መሪ አቶ እውነቱ ታዩ÷ በድሬ ዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውሰጥ ያልተያዙ 90 ከመቶ ለመጋዘንነት እና ለኤክስፖርት ማቀነባበሪያነት የሚያገለግሉ ሼዶች ዝግጁ መሆናቸውን፣ በቀጠናው ውስጥ የድሬ ዳዋ ደረቅ ወደብ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ ማከናወኑን፣ መሰረተ ልማቶች እየተሟሉ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
እስከ ዛሬ የመጣንበት መንገድ ነፃ የንግድ ቀጠናውን እውን ለማድረግ የሚያስችል ምቹ መደላድሎችን የፈጠረና÷ ከመንግስት የሚሰጠው አቅጣጫና ድጋፍ የሚያበረታታ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ነፃ የንግድ ቀጠናው የሎጂስቲክስ ተወዳዳሪነታችንን ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጥ የሚችል መሆኑን ጠቅሰው÷ የተሰሩ ስራዎች በታቀደው የጊዜ ማዕቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠናውን ለመመስረት የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ÷ ድሬ ዳዋ በተዘረጉ የባቡር፣ የመንገድ መሰረተ ልማቶች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና የደረቅ ወደቦች አማካኝነት ነፃ የንግድ ቀጠናውን እውን ለማድረግ ምቹ መሆኗን ጠቁመው÷ የጥናት ቡድኑ የደረሰበት የግምገማና ምልከታ ውጤት ነፃ የንግድ ቀጠናውን ለመመስረት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
መንግስት ነፃ ቀጠናውን ከግብ ለማድረስ ከፍተኛ እገዛ ማድረጉን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.