Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል 4ኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በጋምቤላ ክልል 4ኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በይፋ አስጀምረዋል፡፡
በክልሉ አራተኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በጋምቤላ ወረዳ ቀርሚ ቀበሌ ተጀምሯል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡
አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር በክልሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ ባለፉት አራት ዓመታት በርካታ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸው÷ በዘንድሮው ዓመትም 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ ተይዟል ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡ በተዘጋጁ ቦታዎች ችግኝ በመትከል የተያዘውን ዕቅድ እንዲያሳካም ጥሪ አቅርበዋል።
ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን በመንከባከቡ ረገድም ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡
የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አጃክ ኡቻላ እንደገለጹት፥ በክልሉ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ 25 ነጥብ 73 ሚሊየን ችግኞችን በማዘጋጀት የ2014 በጀት አፈፃፀምን ሳይጨምር 17 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.