Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ የውሃ ፕሮጀክት በተገነባበት አካባቢ ያለ ማህበረሰብን ተጠቃሚ ያደረገውን የውሀ ፕሮጀክት መረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ የመጠጥ የውሃ ፕሮጀክት በተገነባበት አካባቢ ያለ ማህበረሰብን ተጠቃሚ ያደረገውን ወልገኦ አካባቢ የውሀ ፕሮጀክት መርቀዋል፡፡
ፕሪጀክቱ ከዚህ በፊት ይነሳ የነበረውን የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ቅሬታን በመፍታት የጋራ ተጠቃሚነትን ካረጋገጡት የውሃ ፕሮጀክቶች አንዱ ነውም ተብሏል፡፡
የአካባቢው አርሶ አደሮችና የሀገር ሽማግሌዎችም የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በሰራው ስራ አድናቆታቸውን በምረቃ መርሐ ግብሩ ወቅት መግለጻቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከ85 በመቶ በላይ ውሃ የሚያገኘው ከፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በልዩ ዞኑ የሚገኙ ወረዳዎች እና የገጠር ቀበሌዎች 30 መለስተኛ የውሃ ጉድጓዶች፣ 37 የመጸዳጃ ቤቶች እና 105 ለህብረተሰቡ እና ለውሃ የሚሆን የመዳረሻ መንገድ ሰራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አስተዳደሩ አስታውቋል።
የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት በከርሰ ምድር የውሃ ፕሮጀክት ትልቁና የመጀመርያው ሲሆን÷ በተለይ ይህ ፕሮጀክት የአዲስ አበባና አጎራባች ህዝቦችን የጋራ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ በኩል ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.