Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የብስክሌት ሻምፒዮና የፍፃሜ ውድድር በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ቡድን ስፖርተኞችን ለመመልመል እንደሚግዝ የታመነበት የኢትዮጵያ የብስክሌት ሻምፒዮና የፍፃሜ ውድድር በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ውድድሩን÷ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የቴክኒክ ኃላፊ አቶ ግዛቸው መኮንን  እና የድሬ ዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን አመራሮች ናቸው ያስጀመሩት፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የቴክኒክ ኃላፊ አቶ ግዛቸው መኮንን ባደረጉት ንግግር÷ ወድድሩ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኖራትን ቦታ ለማሳደግና ነጥብ ለማስያዝ እንዲሁም ምርጥ የብሔራዊ ቡድን ለመመልመል ያስችላል ብለዋል፡፡

በውድድሩ ላይ ከአዲስ አበባና ከድሬ ዳዋ ከተሞች እንዲሁም ከኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች የተወጣጡ 28 ብስክሌተኞች ከሰኔ 23 ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ውድድራቸውን እያካሄዱ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

እየተካሄደ ያለው የፍፃሜ ውድድም÷ መነሻውን የድሬ ዳዋ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት አድርጎ ዋና ዋና ጎዳናዎችን ያካለለ ሰባት ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን መሆኑ ተመላቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.