Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባህሬን አቋርጦት የነበረውን በረራ ጀመረ

አዲ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁለት ዓመታት በላይ አቋርጦት የነበረውን የባህሬን በረራ ጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ባህሬን ማናማ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት መሪ አምባሳደር አወል ወግሪስን ጨምሮ በባህሬን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ዳዊት እንዲሁምበርካታ ኢትዮጵያውያን ተጓዦች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎለታል።
ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ በመቋረጡ÷ በዜጎች ላይ ሲደርስ የነበረውን እንግልት በእጅጉ የሚቀንስ መሆኑን አምባሳደር አወል ወግሪስ ተናግረዋል፡፡
በዚሁ ዕለት ወደ ኢትዮጵያ ለሄዱ ተጓዦችም የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውን በባህሬን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.