Fana: At a Speed of Life!

ሕግ ሊወጣላቸውና መሻሻል የሚጠይቁ ጉዳዮች ውይይት እየተደረገባቸው ሲወጡ ለሀገረ መንግሥት ግንባታው ጠንካራ ምሰሶ ይሆናሉ- አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕግ ሊወጣላቸውና መሻሻል የሚጠይቁ ጉዳዮች በጥናት እየተለዩ እና ጥልቅ ውይይት እየተደረገባቸው መውጣታቸው ለሀገረ መንግሥት ግንባታው ጠንካራ ምሰሶ እንደሚሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሸገር ተናገሩ፡፡
ፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አመራቶች ጋር በበይነ መንግሥታት የፊስካል ግንኙነት ዙሪያ ሲያካሂድ የነበረው የምክክር መድረክ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡
በመድረኩ የበይነ መንግሥታት የፊስካል ግንኙነት ጥናትና የፖሊሲ አቅጣጫዎች እንዲሁም ውስን ዓላማ ያላቸው የድጎማ በጀት እና የፌዴራል መሠረተ ልማት ስርጭት ፍትሐዊነት የክትትል ሥርዓትን ለማስጸም ረቂቅ ደንብ ለውይይት ቀርበው ግብዓት መሰጠቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሕግ ሊወጣላቸውና መሻሻል የሚጠይቁ ጉዳዮች በጥናት እየተለዩ እና ጥልቅ ውይይት እየተደረገባቸው መውጣታቸው ለሀገረ መንግሥት ግንባታው ጠንካራ ምሰሶ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
ሁለቱ ምክር ቤቶች በተሰጣቸው ሕገ መንግሥታዊ ስልጣንና ኃላፊነቶች መሠረት በጋራ መሥራታቸው÷ የተጀመረውን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ለማጎልበትና በእኩልነት ላይ የተመሠረተ አንድነት ለማሳደግ ትልቅ ድርሻ እንዳለው በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.