Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የጅግጅጋ መብራት ኃይል ማስፋፊያ ፕሮጀክትን መረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ርዕሰ ማሌ ክልል ዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የጅግጅጋ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ማስፋፊያ ፕሮጀክትን በይፋ መርቀዋል፡፡
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ እና የጅግጅጋ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር አብዱላሂ አብሽር ተገኝተዋል፡፡
ከተማዋ ቀደም ሲል 17 ዓመታት ከነበራት12 ሜጋ ቮልት ላይ 31 ሜጋ ቮልት በመጨመር በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 43 ሜጋ ቮልት እንድታገኝ መደረጉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
አቶ ሙስጠፌ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ከለውጡ በኋላ የኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ ለህብረተሰቡ ኑሮ ወሳኝና መሰረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ማሻሻል ላይ በትኩረት እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግስት ላለፋት አራት ዓመታት የሕዝብ ማህበራዊ ልማት የጀርባ አጥንት የሆኑትን የመብራት፣ የውሃና የመንገድ መሰረተ ልማቶች በልዩ ትኩረት መሥራቱንም ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.