Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል ያሰለጠናቸውን የልዩ ኃይል አባላት አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያሰለጠናቸውን የክልል ልዩ ኃይል አባላት አስመረቀ።
ኮሚሽኑ የልዩ ሃይል አባላቱን ለአራት ወራት ነው አሰልጥኖ ያስመረቃቸው።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል እንዳሻው ጣሰው ተገኝተዋል።
ስልጠናው በክልሉ የሚካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ከማድረግ አንፃር ያለውን የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ ያለመ ነው ተብሏል።
ከዚህ ባለፈም የክልሉንና የህዝቡን ፀጥታና ደህንነት በመጠበቅ በክልሉ ያለውን የህግ የበላይነት ለማጠናከር እንደሚያግዝ ከፌደራል ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።.
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.