Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በነገው ዕለት ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በነገው ዕለት በደብረብርሀን ከተማ እንደሚጀመር የሊጉ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
ስብሰባው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ በዋናነት በሊጉ የተሠሩ ሥራዎችን በመገምገም ለቀጣይ ተግባራት አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ተመላክቷል፡፡
በተለይም ምግቤን ከጓሮዬ በተሰኘው መሰል የወጣቶች ንቅናቄ የተሠሩ ሥራዎችን መስክ ድረስ ወርዶ በመጎብኘት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚደረግ የሊጉ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ጎን ለጎን ከስድስት ሚሊየን በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት የ2014 የክረምት በጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እንደሚካሄድም ነው የተገለጸው፡፡
የብልፅግና ፓርቲ አንደኛ የወጣቶች ሊግ ጉባኤ የሚካሄድበት ቀን፣ ወር እና ቦታ በማዕከላዊ ኮሚቴው ውይይት ተደርጎበት እንደሚወሰን የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ፕሬዚዳንት እና የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አክሊሉ ታደሰ ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.