Fana: At a Speed of Life!

የአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦችን የሰላምና ልማት ተጠቃሚ ማድረግ ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በአዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦችን የሰላምና የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በእንጅባራ ከተማ እየመከሩ ነው።
 
መድረኩን የከፈቱት የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው÷ ትናንት የነበረውን አለመግባባት በውይይት በመፍታትና የግጭት መንስኤ የሆኑ አጀንዳዎችን በማስወገድ የአዋሳኝ አካባቢዎች የጋራ የሰላምና የልማት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
 
የህዝቦችን አንድነት በመልካም ግንኙነት ለማሻገር በሚደረገው ርብርብ የአመራሩ ሚና ወሳኝ መሆኑ ነው የተገለጸው።
 
በምክክር መድረኩ በአማራ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ በሆኑ የመተከል ዞንና ወረዳዎች በግብረ ሃይሉ አማካኝነት የተሰሩ የ5 ወራት አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
 
በሁለቱ ክልሎች የጋራ ውይይት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አቢዮት አልቦሮን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮችና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች መገኘታቸውን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.