Fana: At a Speed of Life!

አቶ ርስቱ ይርዳ የክረምት ወቅት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በጉራጌ ዞን እንድብር ከተማ የ2014 የክረምት ወቅት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
በክልሉ 2 ሺ 300 የአረጋውያንን ቤት አፍርሶ ለመገንባት መታቀዱን በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ተመላክቷል፡፡
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷በክልሉ የአረጋውያንን ቤት አፍርሶ ለመገንባት14ሚሊየን ብር በመመደብ እየተሰራ ነው።
በተያዘው በጀት ዓመት ለ2ሺ 300 አረጋውያን ቤቶች እድሳት እና ግንባታ እንደሚካሄድ መናገራቸውንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አቶ ርስቱ ወጣቶች የአባቶቻቸውን የቀደመ ታሪክ መሰረት በማድረግ የጀመሩትን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.