Fana: At a Speed of Life!

የ2ኛው ዙር ከኢድ-እስከ- ኢድ ጉዞ ወደ አገር ቤት መርሐ ግብር ተሳታፊዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁለተኛው ዙር ከኢድ-እስከ- ኢድ ጉዞ ወደ አገር ቤት አከባበር ስነ-ስርዓት ተሳታፊዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው፡፡
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክትር ሙሃመድ እንድሪስ ÷በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለእንግዶች አቀባበል አድርገዋል።
 
አምባሳደር ብርቱካን ዳያስፖራዎች ስለ አገራቸው የተሞላ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል፣በልማት፣ በኢንቨስትመንት በአገር ገፅታ ግንባታ ዘርፍ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
በአገራቸው ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል በዚህ ዓመት በርካታ ቁጥር ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ወደ አገራቸው በመግባት ተሳትፎ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።
 
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክትር ሙሃመድ እንድሪስ በበኩላቸው የሁለተኛው ዙር ከኢድ-እስከ- ኢድ አከባበር በይፍ ተመጀመሩን ገልጸው÷መርሐ ግብሩ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች በአዲስ አባባ አና በክልሎች እንደሚከበር ገልፀዎል።
 
የበደር ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የሙስሊሞች ድርጅት ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ ወርቁ የማህበሩ አባላት ጥሪውን በመቀበል እና በቀጣይ ተሳትፎቸውን ለማሳድ አዲስ አበባ መግባታቸዉን ተናግረዋል ።
 
በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ በሆኑ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የተመሰረተው በድር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ድርጅት ከተመሰረተ ከ22 ዓመት በላይ አስቆጥሯል።
 
በተመሳይ ከካናዳ እና በተለያዩ የውጭ አገራት የሚገኙ የዳያስፖራ የአደረጃጀቶች ጥሪውን ተቀብው ወደ አገራቸው እየገቡ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.