Fana: At a Speed of Life!

በውሃ፣ በምግብ እና ኢነርጂ ዋስትና ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በውሃ፣በምግብ እና ኢነርጂ ዋስትና ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

ጉባዔው ፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርስቲ ከአፍሪካ የውሃ ማኔጅመንት ልኅቀት ማዕከል እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ነው።

በጉባዔው ላይ ከሀገር ውስጥ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሐብታሙ ኢተፋን ጨምሮ ፣ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የጉባዔው ዋና ዓላማ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች በተፈጥሮ እና በውሃ ሐብት አያያዝ እና አጠቃቀም እንዲሁም በኢነርጂ ዋስትና ዙሪያ ያሉ ተሞክሮዎችን እንዲለዋወጡ ማስቻል ነው ተብሏል።

በጉባዔው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሐብታሙ ኢተፋ ኢትዮጵያ የጀመረችው የዕድገት ጎዳና ከግብ እንዲደርስ ያላትን የውሃ ሐብት በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል።

ያለ ውሃ ሃብት ኢነርጂ፣መስኖንና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት ሚኒስትሩ የውሃ ሐብት አስተዳደር ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ ከ100 በላይ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚቀርቡም መጠቆሙን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.