በኮፐንሄገን የታጠቀ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዴንማርክ ኮፐንሄገን የታጠቀ ግለሰብ በከፈተው ተኩስ ሰዎች መገደላቸው የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በደረሰው ጥቃት የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአራት ሰዎች ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡
ፖሊስ ድርጊቱ የተፈፀመበት እና በኮፐንሃገን አቅራቢያ ወደሚገኘው የፊልድ የገበያ ማእከል በደረሰ በ11 ደቂቃ ውስጥ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል፡፡
የከተማዋ ፖሊስ ኦፊሰር የሆኑት ሶሬን ቶማሰን ፖሊስ ጥቃቱ የሽብር ተግባር ነው ብሎ እንደማያምን እና ተጠርጣሪው የአዕምሮ ጤና ችግር እንደሌለበት አስረድተዋል፡፡
ሌሊቱን ሙሉ በተደረገው የማጣራት ስራ ተጠርጣሪው ከሌላ አካል ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚያሳይ መረጃ አለመገኘቱንም ፖሊስ መግለፁን ቢቢሲ እና ስካይ ኒውስ ዘግበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!