Fana: At a Speed of Life!

ከሳዑዲ ዓረቢያ 1ሺህ 59 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን የመመለስ ሥራ በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 59 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመለሱት መካከል÷ 63 ሕጻናት፣ 196 ሴቶች እና 800 ወንዶች መሆናቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢው ድጋፍ እና እንክብካቤ ተደርጎላቸው ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉም ተገልጿል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ÷ 46 ሺህ 384 ኢትዮጵያውያን መመለሳቸውን መረጃው አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.