Fana: At a Speed of Life!

የመድኃኒት አቅርቦትን ለማሻሻል የማያሰሩ የሕግ ማዕቀፎች መሻሻል እንደሚገባቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦትን ለማሻሻል የማያሰሩ የሕግ ማዕቀፎች መሻሻል እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡

የመድኃኒት አቅርቦትን ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በሚመለከት በሐዋሳ ከተማ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት ባህል እና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ አባላት የተገኙ ሲሆን፥ የሐዋሳ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ቅርንጫፍንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ ወይዘሮ ወርቅ ሰሙ ማሞ በዚሁ ወቅት÷ቋሚ ኮሚቴውን ጨምሮ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ፣ በውይይት የዳበረ ጠንካራ እና ትውልድ ተሻጋሪ የሆነ የሚያሠራ፣ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት የሕግ ማዕቀፍ ሊኖረን ይገባል ነው ያሉት፡፡

የሕክምና ግብዓቶች ሳይኖሩ የሕክምና አገልግሎት መስጠት እንደማይቻል የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው÷ ለዚህም በግብዓት አቅርቦት ሰንሰለት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በመሆኑ የሚያሠራ የሕግ ስርዓት መኖሩ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

የተቀላጠፈ የመድኃኒት ግዥ እንዲኖር በተለይም የማዕቀፍ እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጥምረት ግዥ በጋራ ለመፈጸም የሕግ ማዕቀፎችን ማሻሻል እንዲሁም አሰራሮችን ማዘመን አስፈላጊ መሆኑን መግለጻቸውን ከመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.