Fana: At a Speed of Life!

በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለማወቅ የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለማወቅ የሚስችል የ“ሴሮ ፕሪቫለንስ” የዳሰሳ ጥናት ሊጀመር መሆኑን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የባክቴሪያል፣ ፓራሳይቲክ እና እንስሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት እና አጋር ድርጅቶች በጋራ በመሆን የ“ሴሮ ፕሪቫለንስ” የዳሰሳ ጥናት ለማስጀመር የሚያግዝ ለመረጃ ሰብሳቢ ባለሙያዎች እና ተቆጣጣሪዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
የጥናቱ ዓላማ የበሽታውን ስርጭት በሀገር አቀፍ ደረጃ በማወቅ ለህብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከልና ምላሽ፥ ለውሳኔ ሰጪ እና ለባለ ድርሻ አካላት በቂ መረጃ እንዲኖራቸው ማድረግ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ስልጠናውም የመረጃ አሰባሰብ ስነ ስርዓትን ማዕከል ባደረገ መልኩ ባለሙያዎች ከዘመናዊ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች እንዲተዋወቁ እና ጥራት ያለው መረጃ እንዲሰበሰብ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለስልጠናው እና ለሚካሄደው የዳሰሳ ጥናት ከፍተኛውን ድርሻ ለተወጡ÷ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች፣ የአፍሪካ ሲ ዲ ሲ፣ የኦሀዮ ግዛት ዩኒቨርሰቲ እና የዓለም ጤና ድርጅትን አመስግነዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.