Fana: At a Speed of Life!

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ከኒውዚላንድ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የኒውዚላንድ አምባሳደር ሚካኤል ኡፕቶን ጋር በትምህርት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ ስለተጀመረው የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ሪፎርም ስራዎች ላይ ተነጋግረዋል፡፡

ከእንግሊዝኛ ትምህርት ማሻሻያ መርሐ ግብር ጋር በተያያዘም÷ የኒውዚላንድ ኤምባሲ የበጎ ፈቃደኝነት ስራ ላይ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ የኒውዚላንድ አምባሳደር ሚካኤል ኡፕቶን በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፍ ላይ ያለውን ሪፎርም አድንቀው÷ በመርህ ደረጃ የተጀመረውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ መርሐ ግብር በተመለከተም ከአገራቸው መንግስት ጋር በመነጋገር ምላሽ እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡

አገራቸው የሚሰጠውን የነጻ ትምህርት ዕድል እንደሚያሰፉም አምባሳደሩ መግለጻቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.