Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ለተፈናቃዮች ከ50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የእህል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር በተለያዩ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ50ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የእህል ድጋፍ አደረገ።

በአማራ ክልል በተፈጥሯዊና ሠው ሰራሽ ችግሮች ከ11ሚሊየን በላይ ህዝብ መፈናቀሉን የጠቀሱት የክልሉ አደጋ መከላከል ና ምግብ ዋስትና ኮሚሽነር አቶ ዘላለም ልጃለም፥የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ለዜጎች የሚሆን 10 ሺህ ኩንታል እህል ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

የዞኑ አስተዳደር በስሩ ካሉ ወረዳዎች እህሉን መሰብሰቡን የገለጹት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደሪ አቶ ወርቁ ኃይለማርያም ፥ መሰል ድጋፉ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው እስከሚመለሡ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

ክልሉ በአሁኑ ስዓት ካለበት የበጀት እጥረት አኳያ ትርፍ አምራች የሆኑ አካባቢዎች ይሄን መሠል ድጋፍ ማድረጋቸው የሚያስመሰግን ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፥መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ በፍትሃዊነት ለተፈናቃዮቹ እንደሚደርስም ነው የተናገሩት።

የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተፈጥሯዊ አደጋዎች ዜጎች እንዳይፈናቀሉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሩ፥የዚህ ተግባር አካል የሆነው በርብና ጉማራ ወንዞች ላይ ሲከናወን የነበረው አደጋ የመከላከል ተግባር መጠናቀቁንም ገልጸዋል።

በበላይነህ ዘለዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.