Fana: At a Speed of Life!

ከተለያዩ ዓለም አቀፍና አገር በቀል አምራች ኩባንያዎች የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች እየመጡ ነው-ኮርፖሬሽኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ ዓለም አቀፍ እና አገር በቀል አምራች ኩባንያዎች የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች እየመጡ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው ከሚያመርቱ ሁለት አምራች ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ከፓርከር ክሌይ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ክብረዓብ አበራ እና ከአክሻይ ጄን ኩባንያ ስራ አስፈፃሚ አክሻይ ጄይን ጋር ነው የተፈራረሙት፡፡

አቶ ሽፈራው ሰለሞን ÷ከተለያዩ ዓለም አቀፍና አገር በቀል አምራች ኩባንያዎች የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች እየመጡ መሆኑን ጠቁመው÷ኮርፖሬሽኑም ጥያቄዎችን ለማስተናገድ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

የፓርከር ክሌይ እና የአክሻይ ጄይን ኩባንያ ሃላፊዎች በበኩላቸው÷ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በፍጥነት ወደ ስራ ለመግባትና ምርት ለመጀመር እንዲሁም ኤክስፖርትን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክና በአዲስ ኢንዱስትሪ መንደር በቆዳ ውጤቶች ምርት እንዲሁም በባዮ-ጋዝና በባዮጋዝ ማዳበሪያ ምርት ዘርፍ ለመሰማራት ሁለት አምራች ኮባንያዎች ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የተፈራረመው አክሻይ ጄይን ተብሎ የሚጠራ ኩባንያ÷ በ884 ሚሊየን ብር ኢንቨስትመንት በጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ 40 ሺህ ሜትር ስኩየር መሬት በመረከብ በባዮጋዝ እና የባዮ-ጋዝ ማዳበሪያ ምርት ለማምረት ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

ሌላኛው ፒ ሲ ኢ ቬንቸር ማኒፋክቸሪንግ ኩባንያ ደግሞ÷ በ30 ሚሊየን ብር ኢንቨስትመንት በአዲስ ኢንዱስትሪ መንደር 1 ሺህ 150 ሜትር ስኩየር ሼድ ውስጥ የቆዳ ውጤቶችን በማምረት ዘርፍ ስራ የሚጀምር ሲሆን ለ300 ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተመላክቷል፡፡

የሁለቱ ኩባንያዎች የኢንቨስትመንት ካፒታል 914 ሚሊየን ብር ሲሆን÷ ይህም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በማነቃቃት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት መገለጹን ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.