Fana: At a Speed of Life!

የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ከመመገብ በተጨማሪ የስራ እድል መፍጠር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ከመመገብ በተጨማሪ የስራ እድል መፍጠር ጀምሯል፡፡

በዛሬው ዕለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተጠቃሚ የነበሩ ሴቶች በልብስ ስፌት ሰልጥነው ተመርቀው ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከልከተቋቋመ አንድ ዓመት የሆነው ሲሆን÷ማዕከሉ ሲከፈት  ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ ̎እንመግባለን ስንል ስንፍናን  እንዳያበረታታ፣ ከመመገብ  ባሻገር የስልጠና እና የስራ እድል መፍጠሪያ እንዲሆን በትኩረት የምንሰራበት ይሆናል̎  ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ዛሬ በምገባ ማዕከሉ ተጠቃሚ የነበሩ እና በመጋቢነት ሲያገለግሉ የነበሩ እናቶች ሰልጥነው ወደ ሚቀጥለው የህይወት ምዕራፍ በመሸጋገራቸው ከንቲባ አዳነች አቤቤ  የእንኳን ደስ አላችሁ  መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከላት መሰል ስራዎችን አጠናክረው  እንደሚቀጥሉ ገልጸው÷ሌሎች ተባባሪ ወገኖችም በመርሐ ግብሩ በመሳተፍ ለዜጎች የተስፋ ብርሃን እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.