Fana: At a Speed of Life!

የጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች የከተማ ግብርናን ለማዘመን የሚያግዝ የከተማ ግብርና አስተዳደር መረጃ ስርአት አበለጸጉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤና ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የከተማ ግብርና አስተዳደር መረጃ ስርአት አበለጸጉ።

በባለሙያዎቹ የበለጸገው ስርአት የከተማ ግብርናን ለማዘመን የሚያገለግል መሆኑ ታውቋል።

የመረጃ ስርአቱ የቀጥታ ግብርና አስተዳደር የመረጃ ስርአት እና የመሬት ግብርና አስተዳደር የመረጃ ስርአት በሚል በሁለት አይነት መልኩ አገልግሎት የሚሰጥ ነው ተብሏል።

ይህ የመረጃ ስርአት ስለ ጓሮ አትክልቶቹ አጠቃላይ ሁኔታ፣ ስም፣ ቦታ፣ ብዛትና አይነት፣ ስለተተከሉበት ቀን እና ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎች ለባለሙያዎች ለማሳወቅ የሚረዳ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር የላከልን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.