Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በፈረንሳይ በተዘጋጀው የቴክስ ዎርልድ የቴክስታይልና ጋርመንት ኤግዚቢሽን እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ የተዘጋጀው የቴክስ ወርልድ የቴክስታይል እና ጋርመንት ኤግዚቢሽን ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡
 
ቴክስ ዎርልድ በዓለም ግንባር ቀደም ከሚባሉ የቴክስታይል እና የጋርመንት ኤግዚቢሽኖች አንዱ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
 
በዚህ ሳምንት በሚካሄደው ኤግዚቢሽንም ከኢትዮጵያ፣ ከቻይና፣ ከህንድ፣ ከቱርክ ከባንግላዲሽ እና ከሌሎች አገራት የተወጣጡ በርካታ ዓለም አቀፍ የቴክስታይል እና ጋርመንት አምራቾች እንዲሁም በፋሽን ኢንዱስትሪው ገናና ስም ያላቸው ብራንዶች ተሳትፈዋል፡፡
 
ኢትዮጵያም ኤግዚብሽኑ ላይ በ9 ዓለም አቀፍ እና የአገር ውስጥ የቴክስታይል እና ጋርመንት አምራቾች የተወከለች ሲሆን÷ ምርቶቻቸውንም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያስተዋውቁ ይሆናል ፡፡
 
የኢንዱትሪ ሚኒስተር ደኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉታ እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ እንዲሁም በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሔኖክ ተፈራ የተመራ የልዑካን ቡድንም በኤግዚቢሽኑ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
 
በኤግዚቢሽኑ መክፈቻ በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ በኢትዮጵያ ስለሚገኙ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ማብራሪያ መሰጠቱን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.