Fana: At a Speed of Life!

መንግስት አሸባሪው ሸኔን ለመደምሰስ እየወሰደ ያለውን የማያዳግም እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጨፌ ኦሮሚያ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት አሸባሪው ሸኔን ለመደምሰስ እየወሰደ ያለውን የማያዳግም እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጨፌ ኦሮሚያ አስታውቋል፡፡

ጨፌው ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ በኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን ሐዋ ገላን ወረዳ አሸባሪው ሸኔ በንጹሀን ዜጎች ላይ በፈፀመው ጥቃት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘንም ገልጿል።

ጨፌው በመግለጫው ህዝብን ከዚህ አሸባሪ ቡድን ጥቃት፣ እንግልትና ስቃይ ለመታደግ መንግስት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያለው።

ሸኔ በወሰደው ዘግናኝ እርምጃ ንጹሃን ዜጎች መጨፍጨፋቸውን እና በድርጊቱ እጅግ ማዘኑን የገለጸው የጨፌው መግለጫ፥ የአካባቢው ህዝብ በንቃት ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን አሸባሪው ሸኔን በማያዳግም ጠንካራ ዘመቻ ለማስወገድ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንዲደግፍ አሳስቧል።

ጨፌው በአሸባሪው ሸኔ ለተቀጠፉት ዜጎች ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማውና ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንደሚመኝም ገልጿል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.