Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል መንግስት በቄለም ወለጋ በሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መንግስት በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ውስጥ በሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ።

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በሰጡት መግለጫ፥ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ዛሬም ሰላምን በሚሻው ንጹሃን ሕዝባችን ላይ የሞት ጽዋን የሚያዘንብ የጥፋት መልአክ ሆኗል ብለዋል።

ከማንኛውም የሰው ዘር ጋር በሰላም መኖርን፣ ሠርቶ መበልጸግንና አግኝቶ መደሰትን ብቻ የሚሻው የአማራ ሕዝብም ሆነ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ወገኖች ሰላምን በማይሹ የሀገርና የሕዝብ ጠላቶች እንዲህ የመጠቃታቸው ብቸኛው ግብ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማንበርከክ አልመው መሆኑን ገልጸዋል።

በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ውስጥ በሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ ለመላው ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።

ዛሬም ሆነ ነገ የዚህ ችግር ብቸኛው መፍትሔ የሕዝባዊ አንድነት ጠላት እና በጋራ ሠርቶ የማደግ ደመኛ የሆኑ ፀረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሆኑ ሁሉንም ኃይላት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንደ ሕዝብ በአንድነት ታግሎ ማሸነፍ ሲቻል ብቻ መሆኑን አመላክተዋል።

ይህን መሰል ጥቃቶችን በመፈጸም መሪር ሀዘን ላይ የሚጥሉንን ጠላቶቻችንን ታግሎ ለማሸነፍና ለዚህ ጉዳይ ከሥሩ መፍትሔ ለመፈለግ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ድምጽ ይህን ድርጊት በመቃወም የመፍትሔው አካል ሊሆን ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.