Fana: At a Speed of Life!

የጎረቤታችን ኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለሀገራችን ሰላም መስፈን እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ በቃላት አይገለጽም -የጁባ ምክትል ፕሬዝዳንት 

አዲስ አበባ፣ሰኔ 28፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የጎረቤታችን ኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ለሀገራችን ሰላም መስፈን እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ በቃላት አይገለጽም ሲሉ በሶማሊያ የጁባላንድ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ማህሙድ ሰይድ ገለፁ።

በሶማሊያ የጁባላንድን የፀጥታ ሁኔታ ለማጠናከር የአካባቢው የፀጥታ ኃይል አመራሮች ከአፍሪካ ኀብረት የሰላም አስከባሪ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ የጁባላንድ ከልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ማህሙድ ሰይድ  ወንድማማችነታችንን በማጎልበት የቀጣናውን ሰላም ለማረጋገጥ ከሰላም አስከባሪው ጋር ተቀናጅተን እንሠራለን ብለዋል።

የአካባቢያችን ሰላም ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲሻሻል የአልሸባብን ሴራና ተንኮል በመገንዘብ የፀጥታ ኃይሉ ከሰላም አስከባሪው ጋር በመቀናጀት ግዳጁን በአግባቡ እየፈፀመ ይገኛል ብለዋል፡፡

የጎረቤታችን ኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ለሀገራችን ሰላም መስፈን እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ በቃላት እንደማይገለፅም አስረድተዋል፡፡

የሰላም አስከባሪ ሻለቃው ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮንን በበኩላቸው የሶማሊያ ሰላም መስፈን ለኢትዮጵያ ሰላም አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

አልሸባብን ከአካባቢው ለማፅዳት የተደራጀ መረጃ በመለዋወጥ የቀጠናውን ደህንነት በጋራ ልንጠብቅ ይገባል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.