Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ አወገዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ላይ የታቃጣውን የግድያ ሙከራ አወገዙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሱዳን ሕዝብ ሰላሙን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ዋጋ ከፍሎ የሚደነቅ እርምጃ መውሰዱን በፌስቡክ ገፃቸው ገልጸዋል።

እንደዚህ አይነት ክሥተቶች የሱዳንን መረጋጋትና የለውጥ ጉዞ ሊያደናቅፉ አይገባምም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በዛሬው ዕለት በካርቱም ከግድያ መኩራ መትረፋቸው የሚታወስ ነው።

በወቅቱም ካርቱም ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ባጀቡት ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት መፈፁሙን የሀገሪቱ መንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከግድያ ሙከራው በኋላ በትዊተር ገፃቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እና ምንም ነገር ቢፈጠር የለውጡን መንገድ የሚያቆመው እንደሌለ አስፍረዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.