Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሐረማያ ኢፋ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤትን መርቀው ሥራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የሐረማያ ኢፋ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤትን መርቀው ሥራ አስጀመሩ።

በ274 ሚሊየን ብር የተገነባው አዳሪ ትምህርት ቤቱ የተማሪዎች መማሪያን ጨምሮ የአስተዳደር እና የመማሪያ መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት ነው።

የሐረማያ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት በትምህርት ውጤታቸው የላቀ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች ተቀብሎ ያስተምራል ተብሏል።

በአሁኑ ጊዜ ከኦሮሚያ ከተለያዩ አከባቢዎች በላቀ የትምህርት አፈፃፀማቸው የተመረጡ 165 ተማሪዎች ትምህርታቸውን መከታተል የጀመሩ ሲሆን በቀጣይም የቅበላ አቅሙ ከፍ እንደሚል ተገልጿል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ መንግስት የትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅ መሰል ፕሮጀክቶችን መገንባቱን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

በክልሉ ደረጃ እየተገነቡ ያሉት የኢፈ ቦሩ እና የቦረ በሩ ትምህርት ቤቶች በአጭር ግዜ ውጤት እያስመዘገቡ ስለመምጣቸው ነው ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ የተናገሩት።

በዚህ መሠረት ርዕስ መስተዳድሩ የሐረማያ ኢፈ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት ከመረቁ በኋላ በቀጣይ ለሚሰራው የቦረ ቦሩ ትምህርት ቤት የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

በተጨማሪም በአወዳይ ከተማ የተገነባውን የአስተዳደር ሕንፃ መርቀው ሥራ እንደሚያስጀምሩም ተገልጿል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ፣ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሀመድና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.