Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካና ቻይና በንግድ ትስስርና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ማረጋጋት ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካና ቻይና በንግድ ትስስርና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ማረጋጋት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት የለን እና የቻይና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሊው ሂ የባይደን አስተዳደር የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት በቻይና ምርቶች ላይ የታሪፍ ቅነሳ በሚያደርግበት አግባብ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የንግድ እና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ጨምሮ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት የለን ከቻይናው አቻቸው ጋር ባካሄዱት የቪዲዮ ውይይት፥ በዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የሸቀጦች ዋጋ መናር እና የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶች ላይ መክረዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትር ጃኔት የቻይናን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ “ ገበያን ማዕካል ያላደረገ ኢፍትሐዊ” ነው ብለውታል።
ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የአውስትራሊያ – ቻይና ግንኙነት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄምስ ላውረንሰን ለአልጀዚራ በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት፥ “የአሜሪካ ባለስልጣናት ቀደም ብለው ከተናገሩት ብዙም የዘለለ አዲስ ነገር የላቸውም።
“ቁም ነገሩ አሜሪካ ተመሳሳይ ውንጀላዎችን ከመድገም በዘለለለ ምን አዲስና የተሻለ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሀሳብ አቀረበች የሚለው ነው” ብለዋል።
የአንድ ወገን ማዕቀቦችም የቻይናን ፖሊሲዎች እንደማይለውጡ የሚያብራሩት ዳይሬክተሩ፥ እንደ ጃፓን እና አውስትራሊያ ያሉ የቅርብ አጋሮችም ለዓለም የንግድ ድርጅትና ለማሻሻያ ሂደቱ ቁርጠኛ ናቸው ነው ያሉት።
በርካታ የንግድ ሕግ ምሁራን በዓለም የንግድ ድርጅት ውስጥ ማስተካከያ የሚያስፈልገው ሰፊ ክፍተት አለ ብለው ይከራከራሉ፥ ነገር ግን አሜሪካ በዚህ ዙሪያ ፍላጎት እንደሌላት ነው የሚገልፁት።
በውይይቱ በማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ እና በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለቶች መረጋጋት ዙሪያ ግልጽ ምክክር ማድረግ መቻሉን የቻይና ንግድ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ምንጭ ፦ አልጄዚራ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.