Fana: At a Speed of Life!

39ኛው የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባዔ በኬንያ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ልዩ የመሪዎች ጉባኤ በኬንያ እየተካሄደ ነው።
በጉባዔው መሪዎቹ በአካባቢው ሀገራት የሚከሰተውን ድርቅ ማሸነፍ በሚቻልበት ሁኔታ፣ በሠላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጉባዔው ለመሳተፍ ዛሬ ወደ ሥፍራው አቅንተዋል፡፡
ጉባዔውን አስመልክቶ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹትም፥ የዛሬው የኢጋድ ጉባዔ መሪዎቻችን ለሁለንተነናዊ የጋራ ጥቅም ለመቆም፣ የጋራ ተግዳሮቶቻቸውን ላይ ለመምከር እና በጋራ ዕድሎቻቸው ለመጠቀም ያላቸውን ግልጽ ቁርጠኝነት ያሳየ ነው ፡፡
ለችግሮቻችን የሠላም አማራጮችን መፈለግ እንዲሁም ድርቅ ከሚያደርሰው ጉዳት የምንወጣው ያሉብንን ችግሮች በጋራ ተቀናጅተን እና ተባብረን መሥራት ስንችል ነውም ብለዋል፡፡
ለሠላም ዕጦት የሠላም አማራጮችን መፈለግ እንዲሁም ድርቅ ከሚያደርሰው ጉዳት ለመውጣት ተቀናጅተን እና ተባብረን መሥራት ያለብንም እኛው ነን ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.