Fana: At a Speed of Life!

ሰው ተኮር በሆኑ ስራዎቻችን የብዙዎችን እምባ ያበሰ ውጤታማ ተግባር እየሠራን ነው – አቶ ጃንጥራር ዓባይ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰው ተኮር በሆኑ ስራዎቻችን የብዙዎችን እምባ ያበሰ ውጤታማ ተግባር በመስራት ላይ እንገኛለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ተናገሩ፡፡
አቶ ጃንጥራር ዓባይ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ወረዳ 12 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ወገኖችን መኖሪያ ቤት እድሳት አስጀምረዋል፡፡
አቶ ጃንጥራር የቤት እድሳቱን ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ሰው ተኮር በሆኑ ስራዎቻችን የብዙዎችን እምባ ያበሰ ውጤታማ ተግባር በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
በጥፋት ኃይሎች ሴራ ያንዣበበብንን አደጋ መቀልበስ የምንችለው÷ በአንድነት ስንታገላቸው በመሆኑ በጋራ ሆነን ልማታችንን እያስቀጠልን ሰላማችንንም ማስጠበቅ ይገባናል ማለታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ዛሬ ግንባታቸው የተጀመሩ ቤቶችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ብዙአየሁ፣ ተመስገንና ጓደኞቹ እምነ በረድ ሽርክና ማኅበር እንዲሁም አዶኒያስ ኢንተርናሽናል የግል ማኅበር በአጭር ጊዜ ግንባታውን አጠናቀው ለማስረከብ ኃላፊነቱን ወስደዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.