Fana: At a Speed of Life!

በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት በመጠለያ የሚገኙ ዜጎችን ጨምሮ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንሠራለን – የአፍሪካ ልማት ባንክ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አርብቶ አደሮች፣ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችንና በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት በመጠለያ የሚገኙ ዜጎችን ጨምሮ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የተቀረጹ ፕሮጀክቶችን በማስፋትና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሠራ የአፍሪካ ልማት ባንክ አስታወቀ፡፡
የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀጣይ በጋራ በሚኖራቸው ቅንጅታዊ ስራዎች ውጤታማነት ላይ ተወያይተዋል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሚኒስቴሩ÷ የሴቶች፣ ወጣቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት፣ ተሳትፎ፣ መብቶችና ደህንነት ለማረጋጋጥ ግንዛቤ በመፍጠር በህብረተሰቡ ውስጥ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ አስገንዝበዋል፡፡
የገጠርና ከተማ ሴቶች፣ አርብቶ አደር ሴቶች፣ ድርቅና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በተከሰቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ሴቶችን መደገፍ፣ በግብርና ሙያ የተሰማሩ ሴቶችን መደገፍ ዙሪያ ዘላቂ ለውጥ ማምጣት በሚያስችል ሁኔታ ፕሮጀክቶች መቀረጽ እንዳለባቸው ማመላከታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተፈናቅለው በማዕከላት የሚገኙ ሴቶችንና ሕጻናትን ጨምሮ ሌሎች ወገኖችን መደገፍ፣ አማራጭ የኃይል ቁጠባ፣ የሴቶች የገበያ ማዕከላት ግንባታና ተደራሽነት ማሳደግ፣ አማራጭና አዋጭ የኢኮኖሚ መስኮች ላይ መደገፍ፣ የውሃና ሌሎች መሰረተ ልማቶች አቅርቦት ላይ ለመስራት መታቀዱን ጠቁመዋል።
ከዚህ ባለፈም 1 ሚሊየን ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የተቀናጅ የወጣቶች ኢኮኖሚ ፕሮግራም መደገፍ እና አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መፍጠር ላይ በቀጣይ ከባንኩ ጋር በትኩረት ለመስራት ማቀዳቸውን ገልጸዋል፡፡
በአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ምክትል ጄነራል ዳይሬክተር ዶክተር አብዱል ቢ. ካማራ በበኩላቸው÷ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አርብቶ አደሮች፣ ተጋላጭ ህብረተሰብ ክሎችንና በተለያዩ ተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት በመጠለያ የሚገኙ ዜጎችን እና አጠቃላይ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የተቀረጹ ፕሮጀክቶችን በማስፋትና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚኒስቴሩ ጋር በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል፡፡
ባንኩ በቀጣይ እነዚህን ስራዎች የሚከታተልና የሚያስፈጽም የተደራጀ የሰው ሀይል እንደሚያቋቁምም አስታውቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.