Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ እስካሁን በወሰደው እርምጃ 12 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ተወረሱ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እስካሁን ድረስ በተወሰ ሕጋዊ እርምጃ 12 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መወረሳቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ በዛሬው ዕለት ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ የጣሱ ተጨማሪ ሁለት የነዳጅ ቦቴዎችን መውረሱን አስታውቋል፡፡

ቢሮው ከቀናት በፊት መመሪያና ደንብን ያልተከተሉ10 የነዳጅ ቦቴዎችን መውረሱ ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለትም መመሪያና ደንብ የጣሱ ሁለት ተጨማሪ የነዳጅ ቦቴዎች በፀጥታ ኃይሎችና በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዘው እንዲወረሱ መደረጋቸው ተገልጿል፡፡

የከተማው ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ እንደገለጹት÷ 80 ሺህ ሊትር ግምት ያለው ነዳጅ የጫኑ ሁለት የነዳጅ ቦቴዎች ተወርሰዋል፡፡

እስከ አሁን ቢሮው በወሰደው እርምጃ 12 የነዳጅ ቦቴዎችን መወረሳቸውን እና የተወረሰው ነዳጅም በነዳጅ ማደያዎች በኩል መከፋፈሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ሕግ አክብረው በማይሰሩና ሆን ብለው እጥረቱ እንዲባባስ በሚያደርጉ የነዳጅ ኩባንያዎች ላይ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.