Fana: At a Speed of Life!

በትራንስፖርት ባለስልጣን እና በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት መካከል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

 አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን እና በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት መካከል የተቀናጀ የትራንስፖርት አስተዳደር ስርዓትን ማስተግበር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ።
ስምምነቱን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሣ ያደታ እና የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ ተፈራርመውታል።
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የትራንስፖርት ዘርፉን በማዘመንና የአገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የህብረተሰቡን የእርካታ ደረጃ ለማሳደግ ያቀረብነውን ጥያቄ በፍጥነት በመመለሱ አመስግነዋል።
የተቀናጀ የትራንስፖርት አስተዳደር ስርዓትን መተግበር የወጪና የገቢ ንግድ ለማስፋፋት፣ በትራንስፖርት ዘርፍ የሚገኘውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመቅረፍ እና የትራንስፖርት ሎጅስቲክስን ለማዘመን ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልፀዋል።
ለተግባራዊነቱም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም አረጋግጠዋል ሚኒስትሯ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ በበኩላቸው ስምምነቱ ከትራንስፖርት ዘርፉ ባሻገር ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ጥቅም አለው ብለዋል።
በመሆኑም የአቅም ግንባታ ሥራን ጎን ለጎን በማከናወን የእውቀት ሽግግር እንዲፈጠር በማድረግ ለስምምነቱ ውጤታማነትና ተግባራዊነት እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.