Fana: At a Speed of Life!

ፖቼቲኖን ያሰናበተው ፒ ኤስ ጅ ክርስቶፍ ጋልቲዬርን በአሰልጣኝነት ሾመ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳዩ እግር ኳስ ክለብ ፓሪስ ሴንት ጀርመን አሰልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቼቲኖን አሰናበተ።
ክለቡ በትዊተር ገጹ አርጀንቲናዊውን አሰልጣኝ ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል።
ፖቼቲኖ ቶማስ ቱሼልን በመተካት ነበር በፈረንጆቹ 2021 ጥር ወር ላይ የፓሪሱን ክለብ በ18 ወራት ኮንትራት የተረከቡት።
ወደ ፓሪስ ካቀኑ በኋላ ከክለቡ ጋር የሊግ 1 ዋንጫን ማንሳት ቢችሉም ክለቡ የሚፈልገውን የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ማሳካት አልቻሉም።
ከክለቡ የቻምፒየንስ ሊግ ያልተቃና ጉዞ ጋር በተያያዘ አሰልጣኙ ከክለቡ ጋር ይለያያሉ በሚል ጭምጭምታዎች ሲሰሙ ቆይተዋል።
የኒሱ ዋና አሰልጣኝ ክርስቶፍ ጋልቲዬር ፖቼቲኖን በመተካት የፈረንሳዩ ክለብ ቀጣይ አሰልጣኝ መሆናቸው ተረጋግጧል።
ክርስቶፍ ጋልቲዬር ሊል የሊጉ ሻምፒዮን በነበረበት የፈረንጆቹ 2020/21 የውድድር ዘመን የቡድኑ አሰልጣኝ እንደነበሩ ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.