Fana: At a Speed of Life!

በሱዳን የሽግግር መንግስት ለመመሥረት ወታደራዊ ኃይላቸውን እንደሚያስወጡ አል-ቡርሃን ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ወታደራዊ መሪ የሆኑት ጄነራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን በሀገራቸው የሽግግር መንግስት ለመመስረት የሚያስችል መደላድል ለመፍጠር ወታደራዊ ኃይላቸውን ከፖለቲካዊ ውይይቱ እንደሚያስወጡ በትናንትናው ዕለት አስታውቀዋል፡፡

በሱዳን ፖለቲከኞች እና አብዮተኞች የሽግግር መንግስት ለመመስረት ፖለቲካዊ ድርድር እያካሄዱ መሆኑ ተነግሯል፡፡

አልቡርሃን በሀገሪቷ አዲስ መንግስታዊ አስተዳደር ከተመሰረተ በኋላ ሉዓላዊው ምክር ቤቱ እንደሚፈርስም ነው የጠቆሙት።

አል-ቡርሃን በመጨረሻ ይህን ያስታወቁት በሱዳን የዘለቀውን ፖለቲካዊ አለመግባባት ለመፍታት ያለመ ውይይት መካሄድ ከጀመረ ከአንድ ወር በኋላ መሆኑንም ነው ሲ ጂ ቲ ኤን የዘገበው።

በሱዳን የሠላም ማስፈን ተልዕኮው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱዳን የፖለቲካ ተልዕኮ ፣ በአፍሪካ ኅብረት እና በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት አስተባባሪነት ይመራልም ነው የተባለው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.