Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ 130 ሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው አውሮፓ በ22 ሀገራት በተካሄደ የጋራ ዘመቻ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተጠረጠሩ 130 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዓለም አቀፍ የፖሊስ ድረጅት (ዩሮፖል) ዛሬ አስታውቋል።
በፈረንጆቹ እስከ ሰኔ 13 ድረስ በተካሄደውበዚሁ የፖሊስ እርምጃ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች ተለይተው እንዲታወቁ አድርጓል ሲል ዩሮፖል ገልጿል።
በአውሮፓ ኅብረት የድንበር ጉዳዮች ተከታታይ ኤጀንሲ አስተባባሪነት በተደረገው ዘመቻ በተለይም በብዛት ወደ አውሮፓ በሚያስገቡ መንገዶች በባህር፣ በየብስ እና በአየር ድንበሮች ላይ ወደ አንድ ሚሊዮን በሚጠጉ ሰዎች እና 200 ሺህ ተሽከርካሪዎች ላይ ፍተሻዎች ተደርጓል፡፡
በጋራ ዘመቻው ከቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና፣ ሞንቴኔግሮ፣ ሰሜን መቄዶንያ፣ ሰርቢያ፣ ዩክሬን፣ ብሪታኒያ እና ሊችተንስታይን ጋር በመሆን ከአውሮፓ ኅብረት የተውጣጡ 15 ሀገራት ተሳትፈዋል።
ወደ 22 ሺህ 500 የሚጠጉ የሕግ አስከባሪዎች መሳተፋቸውንም የሮይተርስ ዘገባ አመላክቷል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.