Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን እና በተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊነቶች ላይ ያገለገሉት ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ወይዘሮ ነፃነት ከዚህ ቀደም በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ፣ የኢፌዴሪ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዲኤታ እና በሌሎች የስራ ሀላፊነቶች ላይ ሰርተዋል።

በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ ውስጥም የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በወይዘሮ ነፃነት ህልፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወይዘሮ ነፃነት አስፋው ህልፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል።
 
የቀብራቸው ስነ ስርዓት በመቐለ ከተማ የአርበኞች መቃብር ስፍራ የሚፈጸም ይሆናል።

 

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.