Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ያላትን ምቹ ሁኔታ ለመጠቀም ተዘጋጅተናል – የሳዑዲ የግብርናና የእንስሳት አቅርቦት ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ ያላትን ምቹ ሁኔታ ለመጠቀም በግብርና ባለሙያዎች ጥናት መሰረት ወደ ኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ተዘጋጅተናል ሲሉ የሳዑዲ ዓረቢያ የግብርናና የእንስሳት አቅርቦት ድርጅት ዋና መምሪያ ኃላፊ ኢንጅነር ሱለይማን አብዱራህማን አሩመይሒ ገለጹ፡፡

 

አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ከሳዑዲ ዓረቢያ የግብርናና የእንስሳት አቅርቦት ድርጅት ዋና መምሪያ ኃላፊ ኢንጅነር ሱለይማን አብዱራህማን አሩመይሒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

 

በውይይታቸውም ÷ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ እምቅ አቅም ያላት እንደመሆኑ መጠን የሳዑዲ መንግስትም ሆነ የግል ኢንቨስተሮች ኢትዮጵያ ላይ የዘመናዊ የእርሻ ቴክኖሎጂ እና መዋዕለ ነዋያቸውን ኢንቨስት እንዲያደርጉ አምባሳደር ሌንጮ መጠየቃቸውን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ይጠቁማል፡፡

 

ኢንጅነር ሱለይማን አብዱራህማን በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ ያላትን ምቹ ሁኔታ ለመጠቀም ከሁለቱ ሀገራት በተውጣጡ የግብርና ባለሙያዎች ጥናት መሰረት ወደ ኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.