Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ምርቶች በፈረንሳይ ንግድ ትርዒትና ባዛር ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርቶች በፈረንሳይ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒትና ባዛር ላይ ለዕይታ ቀርበዋል፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ ቻይና፣ ህንድ ፣ቱርክ ፣ ባንግላዲሽ እና ሌሎች ሀገራት በአውደ ርዕዩ የተሳተፉ ሲሆን÷ ኢትዮጵያ ዘጠኝ ድርጅቶችን በማሳተፍ የሀገር ውስጥ እና የወጪ ሀገር ምርቶቿን ለዕይታ አቅርባለች፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ ዘርፉን በተመለከተ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመት አማራጮች እና የአምራች ዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን በተመለከተ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱም÷ የአምራች ዘርፉን እድሎች ምቹ ሁኔታዎች ለማስተዋወቅ፣ የአገር ገጽታን ለመገንባት እና ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ለመሳብ አውደ ርዕይው ከፍተኛ ሚና እንዳለው መገለጹን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡልልታ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ቱሬሳ እና በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ በተገኙበት አውደ ርዕዩ ተካሂዷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.