Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጩን ለአምስት ሳምንታት አራዘመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስረታ ላይ የሚገኘው አማራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጩን ለአምስት ሳምንታት አራዘመ።

የአክሲዮን ሽያጩ በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሽያጩ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ዕድል ለመስጠት በማሰብ መራዘሙን የአደራጅ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ አቶ መላኩ ፈንታ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም ሙስሊሙን ማህበረሰብ በስፋት ለማሳተፍና ስለ አክሲዮን ሽያጩ በቂ መረጃ እንዲኖራቸው ለማድረግ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬን በይበልጥ ለማግኘት በማሰብ ተራዝሟልም ነው ያሉት።

ሽያጩ በአቢሲንያ፣ ዳሽን፣ አዋሽ ባንክ እና ንግድ ባንክ እንደሚፈጸምም ገልጸዋል።

ካለፈው ነሃሴ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በተፈጸመ የአክሲዮን ሽያጭ ከ145 ሺህ በላይ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የአክሲዮን ድርሻ መግዛታቸው ተገልጿል።

ከሽያጩ ውስጥ ከ5 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ የተፈረመ ሲሆን፥ 4 ቢሊየን ብር ደግሞ መከፈሉንም አቶ መላኩ አንስተዋል።

ባንኩ አጠቃላይ ጉባኤውን ሚያዝያ 24 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚያካሂድም በመግለጫው ተነስቷል።

በቅድስት ተስፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.