Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የ2014 የበጀት ዓመት የሴክተር መስሪያ ቤቶች ዕቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) የ2014 የበጀት ዓመት የሴክተር መስሪያ ቤቶች እቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ይገኛል።
በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላን ጨምሮ የካቢኔው አባላት ተገኝተዋል።
በግምገማ መድረኩም÷ በዓመቱ በሴክተር መስሪያ ቤቶች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በሚመለከት በክልሉ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሪፖርት ቀርቧል።
ውይይቱ በነገው ዕለትም ቀጥሎ እንደሚካሄድ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.