Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የ40/60 እና የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት 3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
 
ከተማ አስተዳደሩ በነገው ዕለት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለመሆን ተመዝግበው ለሚጠባበቁ የህብረተሰብ ከፍሎች 3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ተኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት እንደሚያካሂድ ተመላክቷል፡፡
 
የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሚመለከታቸው የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮችና ታዛቢዎች በተገኙበት እንደሚካሄድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.