Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጄክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ፕሮጄክቶች ተመረቁ፡፡
 
በቡራዩ ከተማ በ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ከተገነቡ 105 ፕሮጄክቶች ውስጥ 75 ፕሮጄክቶች ተጠናቀው በዛሬው ዕለት የተለያዩ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡
 
በተመሳሳይ በሰበታ ከተማ 470 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 45 የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡
 
በተጨማሪም በባቱ ከተማ በ190 ሚሊየን ብር በላይ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጄክቶች ግንባታቸው ተጠናቆ መመረቃቸው ተገልጿል፡፡
 
የተገነቡ ፕሮጄክቶች ግንባታ መጠናቀቅ እና መመረቅም በማህበረሰቡ ዘንድ ሲቀርብ የነበረውን ቅሬታ የሚቀርፉ መሆናቸውን ከኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.