Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ በሀላባ ዞን የልማት ፕሮጀክቶችን እየመረቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በሀላባ ዞን ከ 94 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶችን እየመረቁ ነው፡፡
ከተመረቁ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል አራት የጤና ተቋማትን ጨምሮ የአስተዳደር ሕንጻዎች እንደሚገኙበት የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳን ጨምሮ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር መሐመድ ኑርዬ እና ሌሎች የክልል አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.