Fana: At a Speed of Life!

ኡጋንዳ ስዋሂሊኛ የሀገሪቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ወሰነች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኡጋንዳ ስዋሂሊኛ የሀገሪቱ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ወሰነች፡፡
የኡጋንዳ ካቢኔ ስዋሂሊኛ ቋንቋ ከስራ ቋንቋነት ባለፈ በአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥም ውሳኔ አሳልፏል።
ስዋሂሊኛ ቋንቋ በኬንያ፣ ሶማሊያ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚነገር ሲሆን፥ አሁን ላይ ከ200 ሚሊየን በላይ ተናጋሪዎች እንዳሉት ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል።
የስዋሂሊ ቋንቋ በዓለም ላይ ብዙ ተናጋሪዎች ካሏቸው 10 ቋንቋዎች መካከል አንዱ መሆኑ ይነገራል።
የአፍሪካ ህብረት አባል ከሆኑ 54 ሀገራት መካከል 24 ሀገራት የመጀመሪያ የስራ ቋንቋቸው እንግሊዘኛ ሲሆን 21 ሀገራት ደግሞ ፈረንሳይኛን በስራ ቋንቋነት ይጠቀማሉ።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.