Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል ከ650 ሺህ በላይ ተረጂዎች ዕርዳታ ማከፋፈሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል በግጭት እና በድርቅ ለተጎዱ ከ650 ሺህ በላይ ወገኖች የምግብ ዕርዳታ ማከፋፈሉን አስታውቋል፡፡

ዕርዳታውን ወደ ክልሉ ያደረሰው በየስድስት ሣምንታት ልዩነት በማጓጓዝ መሆኑን ጠቁሟል።

ባለፈው ሳምንትም ለ80 ሺህ ወገኖች በምግብ አቅርቦት ተደራሽ መሆን እንደቻለ በትዊተር ገጹ አስታውሷል፡፡

በዛሬው ዕለትም የድርጅቱን የአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በሰሜናዊ አፋር ኮኔባ አካባቢ ደርሰው አቅርቦቱን መጋዘን ውስጥ እያራገፉ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.