Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው ዓለም አቀፉ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው ዓለም አቀፉ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተጠናቀቀ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአለም አቀፉ የኢንተርኔት አስተዳደር ዝግጅት የባለ ብዙ ባለድርሻ አካላት አማካሪ ቡድን ስብሰባውን በጄኔቭ እያካሄደ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ዝግጅት ለአማካሪ ቡድኑ ባቀረቡት ማብራሪያ÷ ኢትዮጵያ በቀጣይ አመት የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ለማስተናገድ የሚያስችላትን በቂ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጉባኤውን ለማካሄድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ጠቁመው÷ ጉባኤው በሰላም እንዲጠናቀቅ ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
17ኛው አለም አቀፉ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ከህዳር 19 እስከ 23 ቀን 2015 ዓም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.