Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዩኔስኮ የማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች በይነ መንግስታት ኮሚቴ አባል ሆነች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንሳዊ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች በይነ መንግስታት ኮሚቴ አባል ሆና ተመረጠች፡፡
በፈረንጆች ሐምሌ 5 ቀን እስከ 7 ቀን 2022 በተካሄደው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጥበቃ ኮንቬንሽን አባል አገራት 9ኛ ጠቅላላ ጉባኤ አገራችን የማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች በይነ-መንግስታት ኮሚቴ አባል ሆና መመረጧ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ በበይነ-መንግስታት ኮሚቴው አፍሪካን ከሚወክሉ አገራት መካከል አንዷ ሆና ነው የተመረጠችው፡፡
ኢትዮጵያ በአባልነት ዘመኗ በዩኔስኮ የሚመዘገቡ የማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ሚዛናዊና የዓለማችንን ውበት እና ብዝሃነት የሚያንፀባርቁ እንዲሆኑ ትሰራለች መባሉንም በፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.