Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው የተመራው የከፍተኛ አመራሮች ቡድን የችግኝ ተከላ አካሄደ 

አዲስ አበባ፣ሰኔ 30፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው የተመራው ከፍተኛ የክልልና የዞን አመራሮች ቡድን ከብላቴ ልዩ የግዳጅ ማሰልጠኛ አመራሮችና ሰልጣኞች ጋር በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሂዷል፡፡

በፕሮግራሙ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ የብላቴ ማሰልጠኛ ተቋም ምልምል ሰልጣኞች፣ የፌድራል ፖሊስ ፣መከላከያ እና ደቡብ ፖሊስ አባላት የሀገር ሠላም ከማስከበር ጎን ለጎን ለሀገር ልማት እያደረጉ ላሉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል።

አካባቢው የፍራፍሬ ምርት የሚሰጥ አካባቢ በመሆኑ ከግል ባለሀብቶች ጋር በመተባበር ከ 4 ሺህ በላይ ችግኝኞች እየተተከለ መሆኑን ርዕሰ መስተዳደሩ ገልፀዋል።

ርዕሰ መስተዳደርርስቱ ”እንዲህ ዓይነት ጀግና ልጆች እያሉ ሀገራችን ከያዘችው የልማት  እና እድገት ጎዳና ወደ ኋላ አትመለስም” ማለታቸውን ከወላይታ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳን ጨምሮ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ፣ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ እና ሌሎች የደቡብ ክልልና የወላይታ ዞን ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.